Get Mystery Box with random crypto!

አንድ እህቴን አፋልጉኝ ! ' እህቴ ዮርዳኖስ ተሰማ ትባላለች። ያለችኝ አንድ እህቴ ናት። እድ | TIKVAH-MAGAZINE

አንድ እህቴን አፋልጉኝ !

" እህቴ ዮርዳኖስ ተሰማ ትባላለች።

ያለችኝ አንድ እህቴ ናት።

እድሜዋ ገና 14 አመት ነው።

ግንቦት 8 /2016 ሐሙስ አመሻሽ 12:00 አካባቢ ከአ/አ ኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ አባጃሌ ከተሰኘ ሰፈር እደወጣች አልተመለሰችም።

በእለቱ ከላይ ጥቁር እጅጌ ጉርድ ቲሸርት ከፊለፊቱ ቡራቡሬ ስዕል ያለው እና ከታች ቡና ወይ ሽሮ ከለር መሳይ ስስ ቀሚስ ለብሳ ነበር።

ቤተሰቦቻችን ያሳደጉን በመከራና በእንግልት ነው
እናታችን በጣም እየተጎዳች ነው አትቀመጥም በየቀኑ አገኛታለው ብላ አገር ለሐገር እየዞረች ነው።

እህታችንን ያያት ወይም ያገኛት ከታች በተጠቀሱስ ስልክ ቁጥሮች ቢያሳውቁን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

ስልክ ፦
 0934490756
0925776169
 0923150119
 0970222977 "

@tikvahethmagazine