Get Mystery Box with random crypto!

ኬንያ ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የገዛችው የኤሌክትሪክ ሀይል ከባለፈው አመት በ41 በመቶ ማደጉ ተገለ | TIKVAH-MAGAZINE

ኬንያ ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የገዛችው የኤሌክትሪክ ሀይል ከባለፈው አመት በ41 በመቶ ማደጉ ተገለፀ

ኬንያ ከፈረንጆቹ አዲስ አመት 2024 ጀምሮ ባሉት 3 ወራት ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የገዛችው የኤሌክትሪክ ሀይል ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ41 በመቶ ማደጉን ተገለፀ።

ኬንያ በተጠቀሰው ጊዜ ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ 408.78 Gigawatt-hour (GWh) የገዛች ሲሆን ይህም ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገዛው የ 288.3 GWh የኤሌክትሪክ ሀይል ግዢ በ41.7 የበለጠ መሆኑ ተጠቁሟል።

ለሀይል ግዢው ኬንያ ወደ 4.23 ቢሊየን የኬንያ ሽልንግ ያወጣች ሲሆን የሃይል አቅርቦቱ ርካሽ እንደሆነና ሀገሪቱ ጥገኛ የሆነችበትን የሙቀት ሀይል ማመንጫ ወጪን እየቀነስ መሆኑን ቢዝነስ ዴይሊ አስነብቧል።

@tikvahethmagazine