Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ ኢትዮጵያ ኮሬ ዞን እየተባባሰ በመጣ ጠለፋ ነዋሪዎች ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመ | TIKVAH-MAGAZINE

በደቡብ ኢትዮጵያ ኮሬ ዞን እየተባባሰ በመጣ ጠለፋ ነዋሪዎች ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ተቸግረዋል ተባለ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ውስጥ «እየተባባሰ መጥቷል» ባሉት ጠለፋ የተነሳ ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።

በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ አስተማሪ የሆነ ቅጣት እንደማይሰጥ ያመለከቱት ወገኖች በአሁኑ ጊዜ ሴት ልጆች ወጥተው ለመግባት ስጋት እንደሆነባቸው ዶይቼ ቬለ ዘግቧል።

ስማቸው ያልተገለጸ አንድ አባት ከትምህርት ቤት የምትመለስ ልጃቸው ከሁለት ሳምት በፊት ከትምህርት ቤት እየተመለሰች ሳለ በስድስት ወንዶች ከመንገድ መወሰዷን ተናግረው ጉዳዩን በሕግ ለመፍታት ያደረጉት ጥረትም አለመሳካቱንም አመልክተዋል።

በተጠቀሰው ዞን በያዝነው ግማሽ ዓመት ብቻ ተጠልፈዋል የተባሉ የ24 ልጃገረዶች ሥም ዝርዝር ይፋ መደረጉን ተከትሎ ወላጆችና የህዝብ ተመራጮች በዞኑ የሕግ አካላት ላይ ጫና እያደረጉ ስለመሆኑም ተገልጿል።

@TikvahethMagazine