Get Mystery Box with random crypto!

የ17 አመቷን የግል ተበዳይ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈጸም አንገቷን አንቆ የገደለው ግለሰብ በፅኑ | TIKVAH-MAGAZINE

የ17 አመቷን የግል ተበዳይ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈጸም አንገቷን አንቆ የገደለው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

ከእኔ ጋር በፍቅር ጓደኝነት ለመቀጠል ፈቃደኛ አልሆነችም በሚል የ17 አመቷን የግል ተበዳይ አስገድዶ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈጸም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገ ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ።

አብዱ ኪያር ዩሱፍ የተባለው ተከሳሽ በጳጉሜን 01 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 6፡30 ሰዓት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ሰፈራ ቀርሳ ቢላ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የግት ተነዳይን አንገቷን አንቆ በመያዝ በአካባቢው ወደሚገኝ ካባ በሚወስዳት ጊዜ ላለመሄድ ስትታገለው ነበር።

ግለሰቡ የግል ተበዳይ ጩኸት ስታሰማ በድጋሚ በልብስ ማሰሪያው ጨርቅ አንገቷን አጥብቆ በመያዝና እራስዋን እንዳትከላከል በማድረግ የግብረ-ስጋ ግንኙነት የፈጸመባት እና አንገቷን በእጅ እና በልብስ የወገብ ማሰሪያ ጨርቅ በማነቅ ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።

በዚህም ግለሱቡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶበት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 11ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቶ በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንደሌለው በመግለጹ ፍርድ ቤቱ ለሰራው ወንጀል በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

@TikvahethMagazine