Get Mystery Box with random crypto!

'በትምህርት ቤት ውስጥ ያልተጀመረ ነገር የትም አይደርስም' አቶ ክብረት አበበ የጠብታ አንቡላንስ | TIKVAH-MAGAZINE

"በትምህርት ቤት ውስጥ ያልተጀመረ ነገር የትም አይደርስም" አቶ ክብረት አበበ የጠብታ አንቡላንስ መስራች

በኢትዮጵያ በመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዘርፍ ፈር ቀዳጅ የሆነው የጠብታ አንቡላንስ አዲስ ባቋቋመው ፋውንዴሽን በኩል በአዲስ አበባ ለሚገኙ 10 ትምሀርት ቤቶች በዚህ ዓመት የመንገድ ደኅንነት እና የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ሥልጠና እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የጠብታ አንቡላንስ መስራች አቶ ክብረት አበበ ማክሰኞ ዕለት በህብረት ፍሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ሐሙስ ደግሞ ኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ሥራውን በማስተዋወቅ በይፋ አስጀምረዋል።

አቶ ክብረት አበበ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ?

ጠብታ አንቡላንስ ከምናተርፈው ቀንሰን የማኅበረሰብ አገልግሎት ለማከናወን ፋውንዴሽን (East Afric Emergency Service Foundation) አቋቁመናል። በዚህ ብዙ ሥራዎችን ለመስራት አቅደናል። ይህ ፕሮጀከት አንዱ ነው።

ተማሪዎች ትን እንኳን ቢላቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው መማር አለባቸው። በመኪና አደጋ የወደቀን ሰው በቸልተኝነት ማንሳት ከአደጋው በላይ ገዳይ መሆኑን ማስተማር እንፈልጋለን። በአደጋ የወደቀን ሰው ማንሳት ሳይንስ ነው።

ይህ እውቀት በትምህርት ሥርዓት ውስጥ ተካቶ መሰጠት ያለበት ነው። ይህ ባይሆን እንኳን ከመደበኛው ትምህርት ውጪ መሰጠት አለበት። ለዚህ ትብብር ያስፈልጋል፤ እንስጥ ስንልም መቸገር የለብንም። የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ይህንን ጥረታችንን አይቶ ተባብሮናል።

በትምህርት ቤት ውስጥ ያልተጀመረ ነገር የትም አይደርስም። ሰው ጥሩ ሀኪም የሚሆነው በፍቅር ሲያክም ነው ያንን ፍቅር የምትጨምረው ደግሞ በህጻናት ላይ ነው።

እነዚህ ት/ቤት ቤቶች እኔ የተማርኩባቸው ናቸው፤ ተመልሼ ላስተማረኝ ትምህርት ቤት መስጠት ስላለብኝ ነው ከዚህ የጀመርኩት።

በኢትዮጵያ ከ6 ሚሊዮን በላይ የኮንስትራክሽን ሳይቶች አሉ ተብሎ ይታሰባል። ብዙ ለአደጋ ተጋላጭ ሆኑ የቀን ሰራተኞች በዚህ ሥራ ይሳተፋሉ እነሱን ለማስተማር ተንቀሳቃሽ 100 ኢንች ቴሌቪዥን የተገጠመለት መኪና ሥራ አስጀምረናል። ከስራ በፊት ለ30 ደቂቃ እነሱን ማስተማር እንፈልጋለን።

* በሁለቱም ት/ቤቶች ሮተሪያኖች የተገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ ታንብብ ኢኒሼቲቭ ለትምህርት ቤቶቹ መጽሐፍት አበርክተዋል።

@TikvahethMagazine