Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕዳሴ ግድብ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ 19 ቢሊዮን ብር መዋጣቱ ተነገረ ለሕዳሴ ግድ | TIKVAH-MAGAZINE

የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕዳሴ ግድብ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ 19 ቢሊዮን ብር መዋጣቱ ተነገረ

ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን 193 ቢሊዮን ብር ወጪ የሆነ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እስከ የካቲት 30 - 2016 ዓ/ም ድረስ ለግድቡ 19.2 ቢሊዮን ብር ማዋጣቱን ዶይቼ ቨለ ዘግቧል።

የሕዳሴ ግድብን ቀሪ አጠቃላይ ስራዎች ለማጠናቀቅ 50 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። የሲቪል ግንባታው በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ  እንደሚጠናቀቅ ሲገለፅ የመካኒካል ሥራዎች ደግሞ በ2017 ይጠናቀቃሉ ተብሎ እቅድ መያዙን ተጠቁሟል።

የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎና ድጋፍ አሰባሳቢ ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍቅርተ ታምር የግድቡ አፈፃፀም 95.8 ከመቶ መድረሱን የገለፁ ሲሆን አንዳንድ ሚዲያዎች የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 99.8 ከመቶ ደርሷል ብለው የሚዘግቡት #ስህተት ነው ብለዋል፡፡

@TikvahethMagazine