Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ለአስከፊ ችግር ለተጋለጡ እርዳታ ፈላጊ ዜጎች 1 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ በጄኔቫ ስብሰ | TIKVAH-MAGAZINE

በኢትዮጵያ ለአስከፊ ችግር ለተጋለጡ እርዳታ ፈላጊ ዜጎች 1 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ በጄኔቫ ስብሰባ ሊካሄድ ነው

በመጪው ሚያዝያ 8 በጄኔቫ በኢትዮጵያ አስከፊ የምግብ ዋስትና ችግር በገጠማቸው ዜጎች ጉዳይ ላይ ለመምከር እና ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ በአጋር አካላት እና ሀገራት መሃከል ስብሰባ ሊደረግ መሆኑን ኦቻ አስታወቀ።

ስብሰባው በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ እጅግ አሳሳቢ የሆኑ የምግብ ዋስትና ችግር ለገጠማቸው ዜጎች የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲያገኙ የሚያስችል 1 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ለማሰባሰብ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) በ 2024 በኢትዮጵያ 21 ሚሊዮን ዜጎች የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የገለፀ ሲሆን ለዜጎቹ እርዳታ ለማድረግ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ቀደም ሲል ባወጣው ሪፖርት መግለፁ አይዘነጋም።

@TikvahethMagazine