Get Mystery Box with random crypto!

በካፋ ዞን በጊምቦ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ በካፋ ዞን በጊምቦ ወረዳ ቢጣ | TIKVAH-MAGAZINE

በካፋ ዞን በጊምቦ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

በካፋ ዞን በጊምቦ ወረዳ ቢጣ ጨጋ ቀበሌ ልዩ ስፍራው ዳራ ተብሉ በሚጠራ አከባቢ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ኦባማ የጭነት ተሸከርካሪ ከባጃጅ ጋር በመጋጨታቸው በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድሩሱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በአደጋው ባጃጅ ውስጥ የነበሩ ሾፌሩን ጨምሮ 2 ወንዶችና 2 ሴቶች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲልፍ 1 ሰው ለተጨማሪ ህክምና ወደ ጅማ በመጓዝ ላይ እያለች ህይወቷ ማለፉን ተነግሯል። የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ነውም ተብሏል።

@TikvahethMagazine