Get Mystery Box with random crypto!

ኬንያ የግል የኤሌክትሪክ ሀይል አስመጪዎች ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ሀይል ገዝተው እንዲሸጡ ልትፈቅድ | TIKVAH-MAGAZINE

ኬንያ የግል የኤሌክትሪክ ሀይል አስመጪዎች ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ሀይል ገዝተው እንዲሸጡ ልትፈቅድ ነው ተባለ

ኬንያ በሀገሪቱ በቂ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት እና የሀይል ዋጋ ታሪፍ እንዲቀንስ በማሰብ በሀገሪቱ የሚገኙ የግል የኤሌክትሪክ ሀይል ድርጅቶች ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ሀይል ገዝተው እንዲሸጡ ልትፈቅድ መሆኑ ተነግሯል።

ኬንያ ይህንን ለማድረግ ያቀደችው የኬንያ ኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ቁጥጥር ባለስልጣን (ኢፕራ) በሀገሪቱ ሀይል የሚሸጡ ነጋዴዎችን በማብዛት ለተጠቃሚው ታሪፍ እንዲቀንስ የሚያስችል ሃሳብ በማቅረቡ እንደሆነ ተጠቅሷል። ባለስልጣኑ የኢነርጂ ኤሌክትሪክ ሃይል ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ማውጣቱም ተሰምቷል።

ከዚህ ቀደም ከውጭ ሀገር የኤሌክትሪክ ኃይል ሻጮች ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል የመግዛት ስምምነትን መፈረም የሚችለው የኬንያ መንግስት ብቻ ነው። ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ለኬንያ እየሸጡ ያሉ ሀገራት መሆናቸውም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine