Get Mystery Box with random crypto!

#IMF የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ልዑክ ቡድን ተቋሙ ለኢትዮጵያ ሊያደርገው ባቀደው የብ | TIKVAH-MAGAZINE

#IMF

የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ልዑክ ቡድን ተቋሙ ለኢትዮጵያ ሊያደርገው ባቀደው የብድር ድጋፍ ዙሪያ ለመነጋገር ከመጋቢት 10 ጀምሮ በአዲስ አበባ ያደረገውን የውይይት ጊዜ ማጠናቀቁን አስታውቋል።

በአልቫሮ ፒሪስ የተመራው የተቋሙ ልዑክ የውይይት ጊዜውን ካጠናቀቀ በኋላ በውይይቱ አይኤምኤፍ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ማሻያ መርሃ ግብር ለመደገፍ በሚያስችልበት ሁኔታ ብዙ ለውጥ መታየቱን ገልጿል።

የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም እና ዓለም ባንክ በቀጣይ ወር በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ድጋፉን አስመልክቶ ውይይቱ የሚቀጥል መሆኑንም ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

@TikvahethMagazine