Get Mystery Box with random crypto!

ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል እስከ ደቡብ አፍሪካ የማድረስ ዕቅድ መኖሩ ተገለጸ። | TIKVAH-MAGAZINE

ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል እስከ ደቡብ አፍሪካ የማድረስ ዕቅድ መኖሩ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት እያቀረበች ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል የበለጠ ለማስፋፋት እየሰራች መሆኑን ከኢዜአ በነበራቸው ቆይታ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ለሱዳን፣ ለጅቡቲና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበች መሆኑን ገልጸው፥ ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል እስከ ደቡብ አፍሪካ የማድረስ ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል።

በቅርቡም #ለታንዛኒያ ኃይል ለማቅረብ መግባባት ላይ መደረሱን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ደቡብ ሱዳን፣  ኡጋንዳና ሩዋንዳ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየታቸውንም አንስተዋል።

ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ንግግር መጀመሯን ነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የገለጹት።

@TikvahethMagazine