Get Mystery Box with random crypto!

ባለፋት 6 ወራት ውስጥ 1 ሺህ 358 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል ተባለ። ሰሞኑን | TIKVAH-MAGAZINE

ባለፋት 6 ወራት ውስጥ 1 ሺህ 358 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል ተባለ።

ሰሞኑን የተከሰተውን አደጋ ሳይጨምር በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ብቻ  የመጀመሪያ ስድስት ወራት 1 ሺህ 358 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ዛሬ በነበራቸው መግለጫ፥ 2 ሺህ 672 ሰዎች ደግሞ በመኪና አደጋ ሳቢያ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ውድመት መድረሱንም ገልፀዋል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር ደረጃ በ514 የቀነሰ ቢሆንም የጉዳቱ ልክ አሁንም እጅግ አሳሳቢ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ያሉ ሲሆን ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑ የትራፊክ አደጋዎች የሚደርሱት በአሽከርካሪዎች ምክንያት መሆኑ በመግለጫው ተጠቅሷል።

@TikvahethMagazine