Get Mystery Box with random crypto!

የአፍሪካ ልማት ባንክ ስጋትና በናይጄሪያ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የአፍሪካ ልማት ባንክ ናይጄሪያ፣ | TIKVAH-MAGAZINE

የአፍሪካ ልማት ባንክ ስጋትና በናይጄሪያ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ናይጄሪያ፣ አንጎላ፣ ኢትዮጵያ እና ኬንያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ያለው የኃይል፣ የምግብ እና ሌሎች ሸቀጦች ዋጋ መናር በሀገራቱ ውስጥ አለመረጋጋት ሊፈጥር እንደሚችል አስጠንቅቋል። 

ባንኩ በዓመት ሁለት ጊዜ በሚወጣው የአፍሪካን ማክሮ ኢኮኖሚክ አፈጻጸምን በሚዳስሰው ህትመቱ በ2024 ምንም እንኳን አፍሪካ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ብታሳይም ከላይ በተጠቀሱት ሀገራት ከውጭ ምንዛሬ መውረድና የኑሮ ውድነት ምክንያት ግጭቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ ሲል አስጠንቅቋል።

የኑሮ ውድነት ያሰጋቸዋል ከተባሉት አንዷ በአፍሪካ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ናይጄሪያ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሰላማዊ ሰልፍ እያስተናገደች ነው። ሰልፉን የጠሩት የናይጄሪያ የሰራተኛ ማኅበር (Nigeria Labour Congress) ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ላይ የሚደረግ ነው ተብሏል።

እንደ ሀገሪቱ ስታስቲክስ ቢሮ መረጃ ከሦስት አስር ዓመታት በኋላ በናይጄሪያ የዋጋ ግሽበቱ 30% ሆኖ ተመዝግቧል። የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር ከ12 ሚሊዮን በላይ ተጎጂዎችን ለመደገፍ ቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ በትላንትናው ዕለት ገልጿል።

Source: VOA, AP, Africa News, ADB

@TikvahethMagazine