Get Mystery Box with random crypto!

የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 22 ሚሊየን ዩሮ ሰብአዊ እርዳታ መመደቡን አስታወቀ። የአውሮ | TIKVAH-MAGAZINE

የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 22 ሚሊየን ዩሮ ሰብአዊ እርዳታ መመደቡን አስታወቀ።

የአውሮፓ ኅብረት በድርቅ እና ሌሎች ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ አደጋዎች እና ወረርሽኞችን ጨምሮ በግጭት እና መፈናቀል ምክንያት ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚውል 22 ሚሊዮን ዩሮ (ከ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ) አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።

ይህ መጠን በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ለኢትዮጵያ አንዲሰጥ ከተወሰነው 60.5 ሚሊዮን ዩሮ (3.5 ቢሊዮን ብር) ላይ የተጨመረ ነው ያለው ኅብረቱ በ 2023 ለኢትዮጵያ ያደረገው የሰብአዊ እር ዳታ ድጋፍ 82.5 ሚሊዮን ዩሮ (4.8.ቢሊየን ብር) መድረሱን አስታውቋል።

@tikvahethmagazine