#AddisAbeba
- በመዲናዋ 703ሺህ የተመዘገበ ተሽከርካሪ ይገኛል፤
- በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት 211 ሰዎች ህይወት በመኪና አደጋ ሲያልፍ 991 ከባድና 749 ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
- ከሟቾች ዉስጥም አብዛኛዉ ከ20 እስከ 49 ዕድሜ ክልል ያሉት ናቸው፤
- ከሚያጋጥሙ የሞት አደጋዎች 78 በመቶ ወንድ ሲሆን 22 በመቶ የሚሆነዉ የሞት አደጋ ሴቶች ላይ የሚያጋጥም ነው፤
- በከተማዋ ከሚፈፀሙ የመኪና አደጋዎች 80 በመቶ የሚሆነዉ ደግሞ እግረኞች ላይ ነዉ፤
በስድስት ወራት ውስጥ በተለያዩ የመዲናዋ መንገዶች ላይ በተደረገ ክትትል፦- 17ሺህ 759 ተሽከርካሪዎች ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር፤
- 2698 የደህንነት ቀበቶ ያላደረጉ፤
- 294 ጠጥተው የሚያሽከረክሩ፤
- 4818 ስልክ እያወሩ በሚያሽከረክሩ የትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰደ ተገልጿል።
ይህ የተነገረው የመንገድ ደህንነት ምክር ቤት የስድስት ወራት አፈፃፀም ግምገማና ውይይት ባካሄደበት መድረክ ነው።
#በተጨማሪ
በ2015 ዓ.ም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በጥናት በተለዩ 20 የትራፊክ መብራቶችና አደባባዮች ላይ ግብይት የፈፀሙ እና በልመና ለተሰማሩ ሰዎች ምጽዋት ሲሰጡ የተገኙ አንድ ሺህ 463 አሽከርካሪዎች ላይ ቅጣት ተጥሏል ተብሏል።
@tikvahethmagazine