Get Mystery Box with random crypto!

በአዳማ ሀሰተኛ ደረሰኝ በማተም እና በማሰራጨት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። በገቢ | TIKVAH-MAGAZINE

በአዳማ ሀሰተኛ ደረሰኝ በማተም እና በማሰራጨት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በከተማዋ ሀሰተኛ ደረሰኝ በማተም በማሰራጨት በህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ገልጿል።

ግለሰቦቹ በከተማዋ ህጋዊ ፈቃድ አውጥተው በተሰማሩ ድርጅቶችና እና ሆቴሎች የንግድ ስም በመጠቀም ግብይት ባልተፈፀመበት ግብይት እንደተፈፀመ አስመስለው ሀሰተኛ ደረሰኝ በማተም እና በመሸጥ ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ደርቤ ገልጸዋል፡፡

በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለሁለት ወራት ያክል በተደረገ ክትትል በተለያዩ 35 በሚሆኑ ህጋዊ ድርጅቶች ስም የታተመ ሀሰተኛ ደረሰኝ የተያዘ ሲሆን ዋነኛ የድርጊቱ ተጠርጣሪዎችን እጅ ከፈንጅ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ተብሏል፡፡

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከሀሰተኛ የወጪ እና የገቢ ደረሰኝ ህትመት እና ስርጭት ባለፈ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች፣ የነዋሪነት መታወቂያና ሌሎች ሀሰተኛ ሰነዶችንም ጭምር ሲያዘጋጁ ነበርም ተብሏል።

@tikvahethmagazine