Get Mystery Box with random crypto!

የ50 ዓመት ዕድሜ ካላቸው አንዲት እናት 2.5 ኪ.ግ የሚመዝን የማህፀን እጢ በቀዶ ጥገና ተወገደ። | TIKVAH-MAGAZINE

የ50 ዓመት ዕድሜ ካላቸው አንዲት እናት 2.5 ኪ.ግ የሚመዝን የማህፀን እጢ በቀዶ ጥገና ተወገደ።

የዓለም ገበያ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለአንዲት የ50 ዓመት ዕድሜ ላላቸው እናት 2:00 የፈጀ ተሳካ ቀዶ ጥገና በማድረግ 2.5 ኪሎ ግራም የሚመዝን የማህፀን እጢ እንዲወገድ አድርጓል።

እናቲቱ በአሁኑ ሰዓት በሙሉ ጤንነት ላይ የምትገኝ ሲሆንቀዶ ጥገናው የተመራው በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም በሆኑት በዶ/ር ታደሰ አማካይነት ነው። በሆስፒታሉ እንደዚህ አይነት ከበድ ያለ የማህፀን እጢ ቀዶ ጥገና ሲደረግ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

መረጃው የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ኮሙንኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine