Get Mystery Box with random crypto!

ልመናና የጎዳና የወሲብ ንግድን ያስቀራል የተባለ አዲስ ሕግ ሊወጣ መሆኑ ተነገረ የሴቶችና ማሕበራ | TIKVAH-MAGAZINE

ልመናና የጎዳና የወሲብ ንግድን ያስቀራል የተባለ አዲስ ሕግ ሊወጣ መሆኑ ተነገረ

የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እየተስፋፋ የመጣውን #ልመና፣ #የወሲብ ንግድን ጨምሮ ሌሎች ማሕበራዊ ቀውሶችን ያስቀራል የተባለ “የማህበራዊ ጥበቃ ፈንድ” ረቂቅ አዋጅ እያዘጋጀ መሆኑ ተሰምቷል።

ረቂቅ አዋጁ፦

ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀለት "የማህበራዊ ጥበቃ ፈንድ" ልመናን ለማስቀረት ትልቅ ሚና እንዳለው ተነግሯል። ይህም ረቂቅ ሰዎች በየመንገዱ የመስጠት ልምዳቸውን የሚያስቀር ነው ተብሏል።

በቅርቡ በሚጸድቀው ሕግ የአገር ውስጥና የውጪ ረጂ አካላት በአንድ ቋት ድጋፍ አድርገው ለሚያስፈልጋቸው የማሕበረሰቡ ክፍል እንዲደርስ የሚደረግበት ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑም ተነግሯል። ልመናን የሚጠላ ዜጋ ለመፍጠርም የሥነ ልቦና ግንባታና ድጋፍ የሚሰጥ የሥራ ክፍል ተቋቁሟል።  

የረቂቅ አዋጁ ፋይዳ፦

ልመናን “ለማስቀረት” የሚያስችለው የሕግ ማዕቀፉ ሲጠናቀቅ በአንድ ቋት ሰዎችን መርዳት የሚያስችል ስርዓት የሚዘረጋ ሲሆን፤ ከዚህ ሥርዓት ውጪ የሚደረግ መፅዋት ሰጪም ሆነ ተቀባይ ተጠያቂ እንደሚደረጉ ተነግሯል።

በአዲስ አበባ 88 ሺሕ 960 በልመና ላይ የተሰማሩ ዜጎች እንዳሉ የሚገመት ሲሆን፣ 50 ሺሕ ያህሉ በዋና ከተማዋ ጎዳናዎች እንደሚኖሩ በ2015 መጀመሪያ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡  

አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ተጠናቆ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ ፍትህ ሚኒስቴር መላኩ እንዲሁም በፍትህ ሚኒስቴር ዝርዝር የሕግ ማዕቀፎች እየተዘጋጀ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ የሕግ ማዕቀፎች ተካተው ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተልኮ እንደሚጸድቅም ይጠበቃል ተብሏል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ሬዲዮ

@tikvahethmagazine