Get Mystery Box with random crypto!

በሀረሪ ክልል የተማሪዎች ምገባ ተጀምሯል። በሀረሪ ክልል የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም የክልሉ ትም | TIKVAH-MAGAZINE

በሀረሪ ክልል የተማሪዎች ምገባ ተጀምሯል።

በሀረሪ ክልል የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

ፕሮግራሙ በክልሉ በሚገኙ ገጠርና ከተማ በሚገኙ 67 ትምህርት ቤቶች የተጀመረ ሲሆን፤ በምገባ ፕሮግራሙ በአጠቃላይ 37 ሺህ 194 ተማሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ነው የተነገረው።

በምገባ መርሃግብሩም ከቅድመ መደበኛ እስከ አራተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

መረጃው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

@tikvahethmagazine