Get Mystery Box with random crypto!

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ 65 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ ነው። የኦሮሚያ | TIKVAH-MAGAZINE

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ 65 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ ነው።

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ባለ 65 ወለል ህንፃ ዋና መስሪያ ቤት ለመገንባት ከኳታሩ Engineering Consulting Group(ECG) ጋር ስምምነት ፈፅሟል።

በተጨማሪም ፋይናንሻል ዲስትሪክት የተሰኘ ባለ 47 ፎቅ ህንፃ በአዲስ አበባ ለመገንባትም እንቅስቃሴ መጀመሩንም አስታውሷል።

ባንኩ 18ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ ሲሆን 699 ቅርንጫፎችን በመክፈት ከ10.4 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን አፍርቷል። የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 112 ቢሊየን ብር፤ አጠቃላይ ሀብቱ ደግሞ 137 ቢሊየን ብር መሆኑ ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ያስመረቀው ዋና መስሪያቤቱ ባለ 48 ወለል ያለውና 198 ሜትር ርዝመት አለው። አቢሲኒያ ባንክ በቅርቡ ሜክሲኮ አደባባይ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ጎን ላይ ከፍታው 270 ሜትር የሆነ ባለ 60 ወለል ህንጻ ለመንባት ውል መግባቱ ይታወሳል። አሁን ላይ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ለመገንባት ያቀደው ባለ 65 ወለል ህንጻ በመዲናዋ ትልቁ ህንጻ እንዲሆን ያስችለዋል።

@tikvahethmagazine