Get Mystery Box with random crypto!

የቅዱስ ጴጥሮስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህጻናት የነርቭ ቀዶ ህክምና የሚውል ማሽን ተበርተ | TIKVAH-MAGAZINE

የቅዱስ ጴጥሮስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህጻናት የነርቭ ቀዶ ህክምና የሚውል ማሽን ተበርተለት።

የቅዱስ ጴጥሮስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እስከ መቶ ሺህ ዶላር የሚገመት ለህጻናት የነርቭ ቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚውል ኢንዶሰኮፒክ ሰርድ ቨንትሪከሎስቶሚ (ኢቲቪ) ማሽን ከሪች አናዘር ፋውንዴሽን ተበርክቶለታል፡፡

ማሽኑ ለህጻናት የነርቭ ቀዶ ህክምና በተለይም የነርቭ ዘንግ ክፍተት ህመም (ሃይድሮሴፋለስ) ላለባቸው ህጻናት በእጅጉ አጋዥ እንደሆነ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻም  ዶ/ር መታሰቢያ መስፍን ገልጸዋል።

የሪች አናዘር ፋውንዴሽን ካንትሪ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ያቆብ ሰማን በበኩላቸው ለህፃናት የነርቭ ቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚውል ማሽን እንደ ሀገር #በዘውዲቱና #ጎንደር ሆስፒታሎች ብቻ ይገኝ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል በሶስተኝነት ተረክቦ አገልግሎት ለመስጠት በሂደት ላይ ይገኛል ብለወላል፡፡

የሆስፒታሉ የነርቭ ቀዶ ህክምና ክፍል ኃላፊ  ዶ/ር አብዲ ኤሪሜሎ ማሽኑ ለህጻናት የነርቭ ቀዶ ህክምና በተለይም የነርቭ ዘንግ ክፍተት ህመም (ሃይድሮሴፋለስ) ላለባቸው ህጻናት በእጅጉ አጋዥ እንደሆነ እና ለህጻናቱ ከጭንቅላት ወደ ሆድ በሚዘረጋ ቱቦ ይደረግ የነበረውን ህክምና በማስቀረት የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ የሚያስችል ማሽን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው  አክለውም የህክምና ማሽኑ ለህጻናቱ የተሻለ ህክምና ከመስጠቱ ባሻገር ይህንን ህክምና ለማግኘት የነበረውን ብዙ ወረፋ በማስቀረት እና የአስታማሚ ወላጆችን እንግልት በመቀነስ እንዲሁም በህመሙ ምክንያት ህጻናቱ ላይ የሚደርሱትን ውስብስብ ችግሮችን የሚቀርፍ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

@tikvahethmagazine