Get Mystery Box with random crypto!

ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት አለፈ። በኦሮሚያ ክል | TIKVAH-MAGAZINE

ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በኦሮሚያ ክልል ከህዳር 26 እስከ ጥቅምት 02  ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በተለያዩ አካባቢዎች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ13 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ በ9ሰዎች ላይ ከባድ እና በ6ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በንብረት ላይ የደረሰዉ ዉድመት በገንዘብ ሲተመን ከ300ሺ ብር በላይ እንደሚገመት የተነገረ ሲሆን አብዛኛዎቹ የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት ተሽከርካሪ፣ በህዝብ ማመላለሻ እንዲሁም በሶስት እግር (ባጃጅ) ተሸርከርካሪዎች የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የቀነሰ ሲሆን ፤ የአደጋ መንስኤ ተብሎ የተመዘገበዉ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣የተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር መሆኑን ከብስራት ሬዲዮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine