Get Mystery Box with random crypto!

ለእንስሳት ዘርፍ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን እንስሳት | TIKVAH-MAGAZINE

ለእንስሳት ዘርፍ ባለሙያዎች

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን እንስሳት ዘርፍ ባለሙያዎችን በተመረጡ 43 ከተሞች ተደራጅተው የእንስሳት ዘርፍ ልማቱን የሚያሳድጉ ፓይለት ፕሮጀክቶች ላይ ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም በእንስሳት ዘርፍ የተማሩ እና የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በኅብረት ስራ ማኅበራት በማደራጀት በዶሮ ሥጋ፣  በእንቁላል፣ በወተት ምርት፣ በግመል ወተት፣ በበግ ሥጋ እና በፍየል ሥጋ ምርት እንደሚሰማሩ ይደረጋል ተብሏል።

በመሆኑም በእንስሳት ዘርፍ ላይ የተማሩ ባለሞያዎች በቅድሚያ በየከተሞቹ ባሉ ኅብረት ሥራ ማዳራጃ ባለሥልጣን መደራጀትና በእነሱ በኩል የሚሰጠውን መመሪያ ተከትላችሁ አስፈላጊ በሆነው ሂደት ውስጥ ማለፍ እንደሚገባ ተገልጿል።

@tikvahethmagazine