Get Mystery Box with random crypto!

ለህንፃ ግንባታ በተቆፈረ ጉድጓድ ምክንያት አለት ተደርምሶ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ በቂርቆስ ክ | TIKVAH-MAGAZINE

ለህንፃ ግንባታ በተቆፈረ ጉድጓድ ምክንያት አለት ተደርምሶ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ስሙ 31አምሳ ቆርቆሮ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ዋልያ ኮንስትራክሽን በሚያስቆፍረው የህንፃ መሰረት ድንገት አለት ተደርምሶ የአንድ ግለሰብ ህይወት አልፏል።

የመደርመስ አደጋው የደረሰው ዛሬ ረፋድ 4:30 አካባቢ ሲሆን፤ ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ ታማሚና ከቤት ወጥቶ የማያውቅ እንዲሁም በሰዓቱ ምንም አይነት የቁፋሮ ስራ አለመኖሩ ተጠቁሟል።

ሆኖም ስጋት ስለነበረ በአካቢው የሚኖሩ ሰዎች እንዲነሱ በሚደረግበት ወቅት አደጋው መድረሱ ተገልጿል። የሟች አስከሬን የእሳት አደጋ ሰራተኞች ከፍርስራሽ ውስጥ በማውጣት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ያስረከቡ ሲሆን፤ ወደ ሚኒልክ ሆስፒታል መሸኘቱን ወረዳው አስታውቋል።

@tikvahethmagazine