Get Mystery Box with random crypto!

በከፋ ዞን ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተገኘባቸው ከ350 በላይ ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ። | TIKVAH-MAGAZINE

በከፋ ዞን ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተገኘባቸው ከ350 በላይ ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን በመንግስት መስሪያ ቤቶች እስካሁን በተደረገ ፍተሻ ከሶስት መቶ ሃምሳ በላይ በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተቀጠሩ ሰራተኞች እና የስራ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ እንደገለፁት ከአመራሩ ጀምሮ ጠቅላላ ባለሙያው የትምህርት ማስረጃ እየተፈተሸ ይገኛል፤ በዚህም ገና ከጅምሩ በርካታ ቁጥር ያለው ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እየተገኘ ነው ብለዋል።

የማጣራት ሂደቱ እስከ ዩኒቨርሲቲዎች ድረስ የሚሄድ በመሆኑ ጊዜ እና ሃብት የሚፈጅ ቢሆንም ማጣራቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በየመንግስት መስሪያ ቤት የሚገኙ አካላት የመንግስትን ሃብት ከማባከን ባሻገር ባልተማሩበት ሙያ በሃሰት ማስረጃ ህዝቡ ትክክልኛ አገልግሎት እንዳያገኝ ሲያደርጉ ነበርና ከስራ እና ከደሞዝ ከመታገድ ባሻገር በህግ እንዲጠየቁ ይደረጋልም ብለዋል።

በክልሉ ባሉ ዞኖች የሃሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ፍተሻው ተጠናክሮ መቀጠሉን የዘገበው ሚዛን ፋና ኤፍ ኤም ነው።

@tikvahethmagazine