Get Mystery Box with random crypto!

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በምግብ መከላከል፣ መቆጣጠርና ማከም በአለም አቀፍ ደረጃ በመድኃኒት ህ | TIKVAH-MAGAZINE

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በምግብ መከላከል፣ መቆጣጠርና ማከም

በአለም አቀፍ ደረጃ በመድኃኒት ህክምና ብቻ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ማከም ከባድ ፈተና ውስጥ መውደቁን የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ያሳያል። በአለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከሚከሰት 55 ሚሊዮን ሞት ውስጥ 70% የሚሆነው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ምክንያት ነው።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ በልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች (CVD) ምክንያት የሚከሰት ሞት  ከ 40% በላይ ሲጨምር በስኳር በሽታ ምክንያት የሚከሰት ሞት ደግሞ በ93% ጨምሯል።

ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ውስጥ በልብ ሕመም፣ በደም ግፊት፣ በስትሮክ እና በስኳር በሽታ ከሚሞቱ ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ጤነኛ ባልሆነ ምግብ ወይም የምግብ ስርአት ምክንያት ነው።

በአንጻሩ ደግሞ ጤነኛ ምግብ (የምግብ  ስርአትን) መከተል እንደ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ፣ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት መጨመር ፣ የደም ግፊት፣ የኮሌስተሮል መጨመር፣ የልብ ህመም ፣ ስትሮክ፣ ካንሰርና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል፣ መቆጣጠር፣ ማከም ወይም ህክምናቸውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚያችል አመልክተዋል።

ጤነኛ ምግብና የምግብ  ስርአትን በመከተል እስከ 80% ድረስ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል ብሎም መቀልበስ ይቻላል።

ሁላችንም በየቤታችን ምግብና የአኗኗር ዘያችንን ማስተካከል ከቻልን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታወችንና ተያይዞ ሊከሰት የሚችልን የሞት ቁጥር በእጅጉ መቀነስ እንችላለን።

ሎዛ የስነ ምግብ ማማከርና ህክምና ማዕከል

@tikvahethmagazine