Get Mystery Box with random crypto!

#አዲስአበባ በአዲስ አበባ ባለፉት ሶስት ወራት በትራፊክ አደጋ ከ 1.2 ሚሊዮን ብር በላይ የ | TIKVAH-MAGAZINE

#አዲስአበባ

በአዲስ አበባ ባለፉት ሶስት ወራት በትራፊክ አደጋ ከ 1.2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ደርሷል

በቀለበት እና ከቀለበት ውጭ ባሉት መንገዶች ላይ በተሽከርካሪዎች ግጭት የተነሳ ከ 1,268,000  ብር በላይ የሚገመት የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ 21 ግጭቶች በቀለበት መንገድ በሚገኙ ሀብቶች ላይ ሲደርስ 39 ግጭቶች ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ በአጠቃላይ 60 የሚሆኑ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

በግጭት ጉዳት እየደረሰባቸው የሚገኙት የመንገድ ሀብቶች በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ተገዝተው በምሽት አገልግሎት እንዲሰጡ በተተከሉት የመንገድ ዳር መብራት ምሰሶዎች፣ የአቅጣጫና ርቀት አመላካች ሰሌዳዎች፣ የመንገድ ማካፈያ ግንቦችና የውሃ መውረጃ ቱቦዎችና ክዳኖች ላይ እና ሌሎች ንብረቶች ላይ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethmagazine