Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ ክልል 4155 ህገ-ወጥ የሰራተኛ ቅጥር ተሰረዘ በደቡብ ክልል 4155 ህገ-ወጥ የሰራተኛ | TIKVAH-MAGAZINE

በደቡብ ክልል 4155 ህገ-ወጥ የሰራተኛ ቅጥር ተሰረዘ

በደቡብ ክልል 4155 ህገ-ወጥ የሰራተኛ ቅጥር፣ ዝውውር ምደባና የደመወዝ ማስተካከያዎችን መሰረዙን የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የበጀት ዓመቱን የ11 ወራት እቅድ ክንውን በሶዶ ከተማ በገመገመበት መድረክ ገልጿል።

የቢሮው ሀላፊ አቶ ዘይኔ ቢልካ በውይይት መድረኩ ላይ እንደተናገሩት በመጠናቀቅ ላይ ባለው በ2014 በጀት ዓመት የ 25 ሺህ 990 የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች ፋይል ተመርምሮ 4155 ህገወጥ ቅጥር ፣ ዝውውር ፣ ምደባና የደመወዝ ማስተካከያዎች ተሰርዟል።

በተደረገው የሰራተኞች ፋይል ማጣራት ከ 614 በላይ ሰራተኞች በሀሰተኛ የትምህርትና የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ ተመርምሮ ቅጥራቸው ተሰርዟል።

በበጀት አመቱ በአሰራር ችግሮች ሊባክን የነበረ 82 ሚሊዮን 887 ሺህ 682 ብር ማዳን ችለናል ብለዋል የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘይኔ ቢልካ። (ደሬቴድ)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot