Get Mystery Box with random crypto!

በግሎባል ፈንድ ድጋፍ የተገዙ የህክምና መሳሪያዎች እየተሰራጩ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ ለጤና ሚኒስቴር | TIKVAH-MAGAZINE

በግሎባል ፈንድ ድጋፍ የተገዙ የህክምና መሳሪያዎች እየተሰራጩ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ለጤና ሚኒስቴር በግሎባል ፈንድ ድጋፍ የተገዙ የህክምና መሳሪያዎች ከግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመሰራጨት ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታውቋል።

በተቋሙ የባዮ ሜድካል ኢንጅነር ባለሙያ አቶ የቻለ ሽፈራው የተሰራጩት የህክምና መሳሪያዎች Oxygen concentrator, pulse Oximeter እና Flow splitte መሆናቸውን ጠቁመዋል።

መሳሪያዎቹም ለኦክስጂን ህክምና አገልግሎት ለመስጠትና የኮቪድ-19ኝን ለመከላከልና ለማከም እንዲሁም በሰውነት ውስጥ የሚገኝ የኦክስጂን መጠንን ለመለካት አገልግሎት እንደሚውሉ ባለሙያው አብራርተዋል፡፡

ስርጭቱም በአገልግሎት ተቋሙ ቅርንጫፎች አማካኝነት ለአፋር፣ ለአማራ፣ ለኦሮሚያ፣ ለቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ለሱማሊያ፣ ለጋምቤላ፣ ለሐረርና ለሲዳማ ክልሎች ፣ ለድሬደዋና ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር እየተካሄደ እንደሆነ ተገልጿል።

ከተገዙት የህክምና መሳሪያዎች መካከል 3 ሺህ 426 Oxygen concentrator ሙሉ በሙሉ የተሰራጩ ሲሆን ከ850 pulse Oximeter ወደ 240 እና ከ237 Flow splitter 68 ስርጭት መካሄዱን አቶ የቻለ ገልጸው ቀሪዎቹ በስርጭት ሂደት ላይ እንደሚገኙና በአጠቃላይ 928 ሚሊየን 584 ሺህ 487 ብር የሚገመት ዋጋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot