Get Mystery Box with random crypto!

የገዛ ልጆቻቸውን የደፈሩ ..... ከፍትህ ሚኒስቴር በተገኘው መረጃ፥ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ | TIKVAH-MAGAZINE

የገዛ ልጆቻቸውን የደፈሩ .....

ከፍትህ ሚኒስቴር በተገኘው መረጃ፥ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የነበረው ተመስገን ገረመው ወሩ እና ሰዓቱ በውል በማይታወቅ በ2004 ዓ.ም ልዩ ቦታው ኡራኤል ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የራሱ ልጅ የሆነችውን የ10 ዓመት ህጻን ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈጽሟል፡፡

ይህ ድርጊቱ አልበቃም ብሎ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ቀኑ፣ ወሩ እና ሰዓቱ በልታወቀ በ2006 ዓ.ም የግል ተበዳይ እናት ለስራ ወደ አረብ ሀገር ስትሄድ ሰክሮ በመምጣት በድጋሚ አስገድዶ ደፍሯታል፡፡

ተከሳሽ በችሎት ፊት ቀርቦ ቃሉን ሲጠየቅ ”እኔ ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለቱ ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮችን እና የሰነድ ማስረጃዎችን ለችሎቱ አቅርቦ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም ተከሳሽ ማስተባበል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።

ተከሳሽ ከዚህ በፊት የጥፋተኝነት ሪከርድ የሌለበት߹ የቤተሰብ አስተዳዳሪ߹ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ እና የጤና እክል ያለበት መሆኑ በድምሩ አራት የቅጣት ማቅለያዎች ተይዘውለት በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

የአዊ ብሔረሰብ ዞን ፍትሕ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ደግም፥ ተከሳሽ ታደለ መለሰ የተባለው ግለሰብ በቀን 28/06/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 4:00በ ሚሆንበት ጊዜ አሳቻ ጊዜን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የገዛ እንጀራ ልጁን አስገድዶ ደፍሯል።

የዐቃቤ ሕግን የክስ መዝገቡን አጠናክሮ ለአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን መርምሮ በቀን 01/10/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹንም ሌሎችንም ያስተምራል ያለውን የ9 አመት ጽኑ እስራት ቅጣት አስተላልፏል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot