Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ ( ሰኔ 1/2014 ) አበርገሌ ወረዳ ከግንቦት 9 ጀምሮ እስካኩን ምንነቱ ያልታወቀ ወ | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ ( ሰኔ 1/2014 )

አበርገሌ ወረዳ ከግንቦት 9 ጀምሮ እስካኩን ምንነቱ ያልታወቀ ወረርሽኝ መከሰቱ ሪፖርት ተደርጓል። የዞኑ ጤና መምርያ የችግሩን ምንነት ለማወቅ በርካታ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሄደው የተመለሱ ቢሆንም ነገር ግን ለችግሩ መፍትሔ ለመስጠት ጥረት ያደረገ የለም ብሏል፡፡የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ኪዳት አየለ ስለወረርሽኙ ምንነትና ስለደረሰው ጉዳት ተጠይቀው፤ " 3 ሕፃናት የዕብድ ውሻ በሽታ ዓይነት ምልክት ባለው ሕመም መሞታቸውን፣ እንዲሁም 5 ተጨማሪ ሰዎች የተለየ ምልክት ባለው ሕመም መሞታቸው ሪፖርት ተደርጎልናል " ብለዋል፡፡ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ማስመለስና የአፍ መድረቅ የሕመም ምልክቶች የሚታይባቸው በጥቅሉ 8 ሰዎች መሞታቸውን ሪፖርት መደረጉን ተናግረዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በአፋር ክልል እስከ 1.2 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ለረሃብ የመጋለጥ አደጋ እንዳንዣበበባቸው አመልክቷል። ድርጅቱ ፤ በክልሉ ላሉ 630,000 ሰዎች ወሳኝ የምግብ አቅርቦት ስርጭት እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።ባለፉት 7 ቀናት ውስጥ ከ1,100 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መግባታቸውን አመልከተዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ትላንት በሰጡት መግለጫ ባለፉት 7 ቀናት ውስጥ ከ1,100 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መግባታቸውን ገልጸዋል። ይሄን ተከትሎም የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲያገኙ በማድረጉ ሂደት ውስጥ የታየውን እድገትና ለውጥ አሜሪካ በደስታ እንደምትቀበል ጠቁመዋል። አክለውም፥ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያሉ አስፈላጊ አገልግሎቶች በአስቸኳይ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ መዓዛ መሐመድ እና ሰለሞን ሹምዬ ላይ የቀረበውን ይግባኝ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነገ ሐሙስ ሰኔ 2/2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የምሥራቅ አፍሪካ አገራት በአስርት ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እንደተጋረጠባቸው የዓለም ባንክ ከሰሞኑ አስታውቋል። የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጫና ተደማምሮ አንዳንድ አገራት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ድቀት እያጋጠማቸው መሆኑን ባንኩ ገልጿል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot