Get Mystery Box with random crypto!

ብሔራዊ ባንክ የመመስረቻ መስፈርቱን ላሟሉ ስምንት ባንኮች ፈቃድ ሰጠ። በብሔራዊ ባንኩ የባንክ ቁ | TIKVAH-MAGAZINE

ብሔራዊ ባንክ የመመስረቻ መስፈርቱን ላሟሉ ስምንት ባንኮች ፈቃድ ሰጠ።

በብሔራዊ ባንኩ የባንክ ቁጥጥር ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው በፋይናንስ ዘርፉ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ለውጦችን ተከትሎ በርካታ ባንኮች የመመስረቻ ፈቃድ ለማግኘት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም ባንክ ለመመስረት የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የካፒል መጠንን ከ500 ሚሊዮን ወደ 5 ቢሊዮን ብር ከፍ ማድረጉን አስታውሰው አጠቃላይ መስፈርቱን ላሟሉ ፈቃድ እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዚህ መሰረት የመመስረቻ ፈቃድ ከጠየቁ 25 አዳዲስ ባንኮች መካከል ብሔራዊ ባንክ ያወጣውን መስፈርት አሟልተው ለተገኙ ስምንት ባንኮች ፈቃድ መስጠቱን ተናግረዋል።

በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ካገኙ ስምንት ባንኮች በተጨማሪ ሦስት ባንኮች ፈቃድ የማግኘት ሂደቱን እያጠናቀቁ ሲሆን ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደሚያገኙ ገልጸዋል።

ብሔራዊ ባንክ ከቅድመ ማመልከቻ ሂደት ጀምሮ ፈቃድ ከተሰጠ በኋላ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ገልጸው የምስርታ ሂደቱ ካልተሳካ ለባለአክሲዮኖች ገንዘባቸው ተመላሽ ይሆናል ብለዋል።

በተመሳሳይ አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት ወደ ባንክ እንዲሸጋገሩ በ2012 ዓ.ም ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ያሟሉ ሦስት አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት ወደ ባንክ መሸጋገራቸውን ገልጸዋል። (ENA)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot