Get Mystery Box with random crypto!

#ጤናረቡዕ (ክፍል 2) ርዕስ ፦ የአንጀት ማይክሮባዮምና ጤናማ አንጀት [ ክሮንስ እና ኮላይ | TIKVAH-MAGAZINE

#ጤናረቡዕ (ክፍል 2)

ርዕስ ፦ የአንጀት ማይክሮባዮምና ጤናማ አንጀት

[ ክሮንስ እና ኮላይተስ ኢትዮጵያ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚያቀርብ ]

የአንጀት ማይክሮባዮም በትሪሊዮን የሚቆጠሩ በአንጀት ክፍል ውስጥ የሚኖሩ ረቂቅ ተሕዋስያን ናቸው። እነዚህ  ረቂቅ ተሕዋስያን ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን ብቻ ሳይሆን ፈንገሶች፣ጥገኛ ነፍሳት እና ቫይረሶችን ያካትታሉ።

በአንጀት ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ረቂቅ ተሕዋሲያን ለጤናችን ወሳኝ ለሆኑት በርካታ ተግባራት ተጠያቂ ናቸው፡፡

እያንዳንዳችን ከወላጆቻችን፣ ወንድሞቻችን ወይም እህቶቻችን ወይም የባህር ማዶ ጓደኞቻችን ለየት ያለ የአንጀት ማይክሮባዮም መጠን እና የጤና ሁኔታ  አለን ፡፡

ጤናማ የሆነ የማይክሮባዮም መጠንን ለማጠናከር የአንቲባዮቲክ መድሃኒቶችን አወሳሰድ ማስተካከል ( ሀኪም ያዘዘውን መድሀኒት ብቻ መውሰድ) አንዱ መንገድ ነው።

ስለ የአንጀት ማይክሮባዮም፣ ጠቀሜታቸውንና ይበልጥ ለማጠናከር የሚረዱ የጤና ምክሮችን በ #InstantView ያንብቡ https://telegra.ph/Gut-Microbe--Healthy-Gut-05-31 ያንብቡ።

በጉዳዩ ላይ ለሚኖሮት ጥያቄ፣ ምክርና አስተያየት በስልክ +251965662501 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @IBDETHIOPIA ላይ ይጻፉልን።

#ዕሮብንለአንጀትጤና

@tikvahethmagazine @ibdeth