Get Mystery Box with random crypto!

#WeeklyUpdate ባሳለፍነው ሳምንት 102 ነጥብ 8 ሚሊዮን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና | TIKVAH-MAGAZINE

#WeeklyUpdate

ባሳለፍነው ሳምንት 102 ነጥብ 8 ሚሊዮን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 26 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹ መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ አዲስ አበባ ኤር ፖርት ፣ እና አዲስ አበባ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 37 ነጥብ 9 ሚሊዮን ፣ 16 ነጥብ 7 ሚሊዮን እና 14 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ተብሏል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot