Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ (ግንቦት 20/2014) ከሰሞኑ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች እና የመ | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ (ግንቦት 20/2014)

ከሰሞኑ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን ቁጥር 19 ደርሷል።

" ሮሃ ሚዲያ " የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነችው መዓዛ መሐመድ ዛሬ ጠዋት በፖሊስ ተይዛ መወሰዷን የስራ ባልደረባዋ እና ጓደኛዋን ዋቢ አድርጎ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ " ዘግቧል።

ትላንት ከሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው “ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል” ተጠርጥሮ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቧል። ያለ ጠበቃ የቀረበው ጋዜጠኛ በቃሉ “ጉዳዩ መታየት ያለበት በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሰረት ነው” ሲል ተከራክሯል። የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፖሊስ በጋዜጠኛው ላይ ለሚያደርገው ምርመራ 12 ቀናት ፈቅዷል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ከተማ አስተዳደር ዳሸን ስሚንቶ ፋብሪካ አካባቢ ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ አምስት ሰዓት አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዋች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

እናት ፓርቲ አራት አመራሮቹ በአማራ እና በደቡብ ክልል ከየሚሠሩበት ቦታ በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወስደው የደረሱበትን ማወቅ እንዳልቻለ ገልጾ እንደነበር ይታወሳል። ፖርቲው ከአራቱ ሁለቱ ስላሉበት ሁኔታ መረጃ እንደደረሰው ገልጾ ቀሪ ሁለቱ ግን እስካሁን ያሉበትን ማወቅ እንዳልቻለ አስታውቋል። አክሎም፥ በየቦታው የሚሳደዱ፣ የሚታፈኑ፣ የሚገደሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሓን ኢትዮጵያውያን ኹኔታ በእጅጉ እያሳሰበን መጥቷል ብሏል።

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በፈረንሳይ ርዕሰ መዲና ፓሪስ በሚገኘው ስታድ ዴ ፍራንስ ስታዲየም ሲካሄድ ሪያል ማድሪድ ከ ሊቨርፑል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 - 0 በሆነ ውጤት በአሸናፊነት አጠናቋል። የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግብ ቪኒሰስ ጁኒየር አስቆጥሯል። ሪያል ማድሪድ ለአስራ አራተኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot