Get Mystery Box with random crypto!

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ወደመ። በጉለሌ ክ/ከተማ | TIKVAH-MAGAZINE

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ወደመ።

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አባዲና ፊትለፊት ባሉ መኖሪያ ቤቶች ላይ ምክንያቱ ያልታወቀ የእሳት አደጋ ተከስቶ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ወድሟል። እስካሁን አደጋው በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም።

በአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞችና 13 ተሸከርካሪዎች በቦታዉ ላይ ተገኝተዋል።

ከቀኑ 6፡30 አካባቢ የተከሰተው ይህ አደጋ ከእሳት አደጋ ሰራተኞች በተጨማሪ የአዲስ አበባ ፖሊስ የፌደራል ፓሊስ እና የአከባቢው ነዋሪዎች ርብርብ በማድረግ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጉለሌ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot