Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ እንዲሆን ተወስኗል በሚል የወጣውን መረጃ አስተዳደሩ አስተባበ | TIKVAH-MAGAZINE

የአዲስ አበባ ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ እንዲሆን ተወስኗል በሚል የወጣውን መረጃ አስተዳደሩ አስተባበለ።

በከተማው ለሚገኙ ሕንፃዎች ቀለማቸው ወጥ የሆነ ስታንዳርድ ለማዘጋጀት ላለፈው አንድ ወር ጥናት ተደርጎ አብዛኞቹ ሕንፃዎች ቀለማቸው ግራጫ ቀለም ያላቸው መሆኑን መረጋገጡንና የአዲስ አበባ ከተማ ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ እንዲሆን መወሰኑ የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ መናገራቸው ተዘግቦ ነበር።

ሆኖም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ ይህንን ጉዳይ አስተባብለዋል። እስካሁን ድረስ የከተማዋ ህንጻዎች ቀለም ምን አይነት ይሁን የሚለው ጉዳይ ለውይይት ቀረበ እንጂ የከተማ አስተዳደሩ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ውሳኔ እንዳላሳለፈ ለኢፒድ ገልጸዋል፡፡

ከተማዋ ላይ አንድ አይነት ቀለም ብቻ ለቀለም ቅብ ሥራ ያስፈልጋል የሚል እሳቤ መያዝ እንደሌለበት የተናገሩት ኃላፊ፤ ለአስፈላጊው ህንጻና አካባቢ የሚመጥን ዝብርቅርቅ ያልሆነና ለዓይን የሚማርኩ ቀለማትን የያዘ ስታንዳርድ እንደሚኖረን ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።

ውሳኔው የከተማው ነዋሪ ምክርና ስምምነት ያስፈልገዋል፤ በሂደቱ ላይም በርካታ ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉና ተወያይቶ መግባባት ላይ መድረስን እንደሚጠይቅ ኃላፊው ጠቁመዋል።

ኃላፊው ጉዳዩን ''በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው'' በሚል የገለጹ ቢሆንም የዚህ መረጃ ምንጭ ግን ሪፖርተር ጋዜጣ በረቡዕ ዕትሙ የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ አቶ ስጦታው አካለን ጠቅሶ ያወጣው ነው።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot