Get Mystery Box with random crypto!

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ  የአያት መንድር ነዋሪዎች ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ እየፈረሰ ነው በአዲስ | TIKVAH-MAGAZINE

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ  የአያት መንድር ነዋሪዎች ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ እየፈረሰ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍል ከተማ  አያት መንድር የዞን 8 ነዋሪዎች ሕጋዊ ካርታ አውጥተው ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ ያለ ምንም ማስጠንቀቂና ሕጋዊ ማስረጃ በትራክተር እየታረሰ መሆኑን ፓርኩን ያለሙት የመንደሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል ሲል አዲስ ማለዳ ዘግቧል፡፡

እንደነዋሪዎቹ ገለጻ ከሆነ፣ ከ15 ዓመት በላይ ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ ወይም ፓርክ ከነዋሪዎች በተዋጣ ገንዘብ በአረንጓዴ ልማት የተሸፈነና የሸክላ ሴራሚክስ የተነጠፈለት ነው፡፡

ይሁን እንጅ ዛሬ ማለዳ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘን ነው የመጣነው ያሉ ፖሊሶች ከ20 እስከ 30 የሚደርሱ ሰራተኞችና አንድ ትራክተር አሰማርተው ፓርኩን እያፈረሱ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ሕጋዊ ካርታ አውጥተው ከ15 በላይ በመናፈሻነት የተጠቀሙት ፓርክ እንደሚፈርስ ምን አይነት ማስጠንቀቂያም ይሁን መረጃ እንዳልተሰጣቸውም ጭምር ነው የተናገሩት፡፡

የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘን ነው የምናፈርሰው ያሉት የመንግሥት አካላት ማዘዣውን ለፓርኩ ባለቤት ለሆኑት ነዋሪዎች እንዲሳዩ ቢጠየቁም የፍርድ ቤት ማዘዣ ማሳየት አልቻሉም ተብሏል፡፡

ፓርኩን የሚጠቀሙ ከ400 በላይ አባዋራዎች ሲሆኑ፣ ፓርኩን ያለሙት ሕጋዊ ካርታ በማውጣትና ብር በማዋጣት እስከዛሬ ድረስ በጋራ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል፡፡ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ከመንግሥት በኩል የተሰጠ አስተያየት በዘገባው አልተካተተም።

@tikvahethmagazine