Get Mystery Box with random crypto!

በህገ- ወጥ መንገድ 7 ሕፃናቶችን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ። ከካፋ ዞን ጨ | TIKVAH-MAGAZINE

በህገ- ወጥ መንገድ 7 ሕፃናቶችን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ከካፋ ዞን ጨና ወረዳ ባላ ሻሻ ቀበሌ ከአስር ዓመት በታች የሆኑ ሰባት ሕፃናቶችን ከሚኖሩበት ቤተሰብ ከብቶችን ትጠብቃላችሁ በማለት አታሎ 7 ሕፃናቶችን በህገ- ወጥ መንገድ ሊያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ ህጻናቶቹን ወደ ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ጉፍቃ ቀበሌ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 በተሽከርካሪ ህፃናቶቹን ይዞ በመጓዝ ላይ እንዳለ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@tikvahethmagazine