Get Mystery Box with random crypto!

የጎዳና ልጆችን ህይወት ለመለወጥ ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ። በአዲስ አበባ 60ሺ ህፃናትና ታዳጊ | TIKVAH-MAGAZINE

የጎዳና ልጆችን ህይወት ለመለወጥ ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

በአዲስ አበባ 60ሺ ህፃናትና ታዳጊ የጎዳና ተዳዳሪዎች እንደሚገኙ የተጠቆመ ሲሆን በመላ ሀገሪቱም የጎዳና ተዳዳሪዎች ቁጥር 150ሺ እንደሚገመት ተነግሯል፡፡

ይህንን የሃገር ውስጥ የህፃናት ፍልሰት ለማስቆም እና ከጎዳና ህይወት ለማስወጣት እንዲሁም ኑሮን ለማሻሻል የሚያስችል ፕሮጀክት በኤስ ኦ ኤስ ህፃናት መንደር ኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅት ይፋ ሆኗል ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ የወላጅ ጥበቃና እንክብካቤ ያላገኙ ህፃናትን መሰረታዊ ፍላጎት ከማሟላት ጎን ለጎን ህፃናቱ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ ቤተሰብ እንዲያገኙ በማድረግ የቤተሰብ ምስረታ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል፡፡

እንዲሁም የአደራ ቤተሰብ፣ ተቋጥሮ ዝምድና ቤተሰብ እንዲሁም ትንንሽ ቤተሰብ የተሰኙ የቤተሰብ ማጠናከሪያና ልማት ፕሮግራሞችን ቀርፆ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

ኤስ ኦ ኤስ ህፃናት መንደር በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና አዳማ ከተሞች የሚተገበረው ፕሮጀክቱ 9000 የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናትን ለመደገፍ የ4 ሚሊዮን ዩሮ መድቧል።

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ ሀገራት ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ዩጋንዳ ሀገራት ለመተግበር 30 ሚሊየን ዩሮ ተመድቦለታል።

Credit : Nahoo TV, MoWSA

@tikvahethmagazine