Get Mystery Box with random crypto!

ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮቪድ 19 ተጠቂ መገኘቱን ይፋ አደረገች። ሰሜን ኮሪያ በሀገሪቱ የ | TIKVAH-MAGAZINE

ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮቪድ 19 ተጠቂ መገኘቱን ይፋ አደረገች።

ሰሜን ኮሪያ በሀገሪቱ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን በዛሬው እለት ይፋ አድርጋለች በሀገሪቱ የተገኘው የኮሮና ቫይረስ ዝርያም አዲሱ “ኦሚክሮን” መሆኑን የሀገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ይህንን ተከትሎም የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በመላው ሀገሪቱ ጥብቅ የሆን የእነቅስቀሴ ገደብ እንዲታወጅ ማዘዛቸው ተሰምቷል።

የሃገሪቱ የቴለቪዥን ጣቢያም ላለፉት ሁለት አመታት ጥበቃ የተደረገበት የድንገተኛ ወረርሽኝ መከላከያ ተጥሷል ብሏል።

የበርካታ ሃገራትን ኢኮኖሚ ያናጋው ኮሮና ቫይረስ በሰሜን ኮሪያ ከዚህ ቀደም ተከስቶ እንደማያውቅ ቢቢሲ ዘግቧል።

የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርትም 24 ነጥብ 7 ሚሊየን ህዝብ ባላት ሰሜን ኮሪያ እስካሁን ከ64 ሺህ 207 ሰዎች ላይ ናሙና ተወስዶ ሁሉም ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ገልጿል።

@tikvahethmagazine