Get Mystery Box with random crypto!

የአፋን ኦሮሞ እና የትግረኛ ቋንቋዎች በGoogle Translate ሥርዓት ውስጥ ተካተቱ። የተለያ | TIKVAH-MAGAZINE

የአፋን ኦሮሞ እና የትግረኛ ቋንቋዎች በGoogle Translate ሥርዓት ውስጥ ተካተቱ።

የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚተረጉመው Google Translate ተጨማሪ 24 ቋንቋዎችን ወደ ሥርዓቱ ማስገባቱን አስታውቋል። ከዚህ ውስጥም የአፋን ኦሮሞ እና የትግረኛ ቋንቋዎች መካተታቸው ተገልጿል።

አዲስ ከተካተቱት ቋንቋዎች ጋር ተደምሮ አገልግሎቱ 133 የዓለም ቋንቋዎችን መተርጎም ያስችለዋል ተብሏል። ከዚህ ቀደም የአማርኛ ቋንቋ በስርዓቱ ውስጥ ተካቶ አገልግሎት ላይ መዋሉ ይታወሳል።

ይህ የትርጉም አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ትክክልኛ ትርጉም ባይሰጥም በተወሰነ ደረጃ የጹሑፎችን ሀሳብ ለመረዳትና ለመጠቀም ይሆናል።

ድርጅቱ ይህንን አገልግሎት ይፋ ያደረገው በትላንትናው ዕለት ሲሆን እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ለሁሉም ተጠቃሚዎች ተደራሽ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethmagazine