Get Mystery Box with random crypto!

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በዩኒቨርስቲው በገንዘብ ዲግሪ ይሸጣል የሚለው መረጃ በመጀመሪያ ባደረኩት ማጣራ | TIKVAH ETHIOPIA

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በዩኒቨርስቲው በገንዘብ ዲግሪ ይሸጣል የሚለው መረጃ በመጀመሪያ ባደረኩት ማጣራት ሀሰት ነው አለ

አዲስ ማለዳ መስከረም 14/2015ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን አስመልክቶ ካወጣው ዘገባ ጋር በተያያዘ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተገቢውን የማጣራት ስራ በማድረግ በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ ኮሚቴ ተዋቅሮ በ18/01/2015 ዓ.ም ስራውን ሲያጣራ ውሏል።በማጣራት ስራው ሂደት ላይ ከዩኒቨርሲቲው Student Information Management System (SIMS) የመረጃ ቋት ላይ በሁሉም ኮሌጆች በመደበኛው፣ በሳምንት መጨረሻ፣ በክረምትና  በማታው የትምህርት መርሀ-ግብር የተመረቁትን ተማሪዎች መረጃ ከመረጃ ቋቱ ላይ በማውረድ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ካጸደቀው የተመራቂዎች ዝርዝር ቃለ-ጉባኤ ጋር የማነጻጸር ሥራ ሰርቷል፡፡

በዚህም መሰረት አዲስ ማለዳ ባወጣው ጋዜጣ የገለፀው እና ምክትል ዋና አዘጋጇ ወ/ሪት ሊዲያ ተስፋዬ በ18/01/2015 ዓ.ም ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል የሠጡት መረጃ መነሻ ተደርጎ ማጣራቱ ተጀምሯል፡፡ ምንም እንኳ ምክትል አዘጋጇ በ18/01/2015 ዓ.ም  በስልክ በሰጡት መረጃ ‹‹የ2014 ዓም  በማኔጅመንት የትምህርት ክፍል  የተመረቁትን አጣሩ›› ያሉ ቢሆንም ባለፉት አራት አመታት በሀገራችን የስርዓተ-ትምህርት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ በ2014ዓ.ም በመደበኛው መርሃ-ግብር በማኔጅመንት ፕሮግራም የተመረቁ ተመራቂዎች አለመኖራቸውን ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡ በአንጻሩ አዲስ ማለዳ ‹‹ሁለት ወራት አጣርቼ አረጋግጫለሁ›› ብሎ ያወጣው ዘገባ እውነት ስለመሆኑ አንድም ፍንጭ አልተገኘም፡፡


#ወልቂጤ ዩንቨርሲቲ

@tikvahethiopianss
@tikvahethiopianss