Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገለፀ ለከፍተ | TIKVAH ETHIOPIA

የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገለፀ

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ለሚወስዱ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስታውቋል ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የመፈተኛ ተቋማት በማዘጋጀት በኩል ግብረሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መመሪያ ሀላፊ አ/ቶ ጌታሁን ፈንቴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። በዞኑ ተማሪዎች የሚፈተኑባቸው አምስት ተቋማት እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር መገለፁ ይታወቃል ።


#ዳጉ_ጆርናል