Get Mystery Box with random crypto!

#Somalia #Ethiopia የሶማሊያ ኘሬዝደንት ሃሰን ሼክ መሃሙድ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብ | TIKVAH ETHIOPIA

#Somalia #Ethiopia

የሶማሊያ ኘሬዝደንት ሃሰን ሼክ መሃሙድ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የሶማሊያ ኘሬዝደንት ሃሰን ሼክ መሃሙድ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር ) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሃሰን ሼክ መሃሙድ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱ ሃገራት እና ቀጠናዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ሼክ መሃሙድ ከስስት ወራት በፊት በተደረገ ምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣን የመጡ ሲሆን በወቅቱ የደስታ መልዕክት ከላኩ መሪዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በቀዳሚነት ተጠቃሽ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ፕሬዜዳንቱ ምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ በተለያዩ ሀገራት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል።

Photo Credit : የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopianss