Get Mystery Box with random crypto!

#Rwanda #UK ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘች | TIKVAH-ETHIOPIA

#Rwanda #UK

ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ዕቅድ የሃገሪቱ ሕግ ሊሆን እንደተቃረበ ቪኦኤ ዘግቧል።

የዕቅዱ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስደተኞቹን #በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እገዳ ተጽዕኖ ለማስቀረት እና በላይኛው ምክር የቀረበውን ተቃውሞ ለመቋቋም የታለመው ይህ ሕግ በዚህ ሳምንት በሃገሪቱ ፓርላማ ይድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

‘ የሩዋንዳ ዕቅድ ’ የሚል ቅጽል የተሰጠው ይህ ውጥን ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ‘ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደዚያች አገር የሚያጓጉዙ ጀልባዎች እንቅስቃሴ’ ለማስቆም ለገቡት ቃል ‘ወሳኝ እርምጃ ነው’ ተብሏል።

የሱናክ ቃል አቀባይ ዴቭ ፓሬስ ምን አሉ ?

" የእንግሊዝ ፓርላማ በያዝነው ሳምንት በሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ከፍተኛ እንግልት እና ብዝበዛ የሚፈጽምባቸውን ሰዎች ህይወት የሚታደግ ህግ የማጽደቅ እድል ያገኛል።

አሁን ባለው አካሄድ መቀጠል እንደማንችል ግልፅ ነው። በመሆኑም ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት ጊዜው አሁን ነው። " ብለዋል።


በአነስተኛ ጀልባዎች ተጓጉዘው የእንግሊዝ ቻናልን በማቋረጥ ከዚያ የሚደርሱትን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሩዋንዳ ለማዛወር እና በቋሚነትም ኑሯቸውን በዚያ እንዲያደርጉ በማቀድ ሁለቱ አገሮች የተፈራረሙት ስምምነት 2 ዓመታት አስቆጥሯል።

በፍርድ ቤት የታገደው ዕቅድ እንግሊዝን በትንሹ 470 ሚሊዮን ዶላር ሊያስወጣት እንደሚችል ቪኦኤ በዘገባው አስፍሯል። #VOA

@tikvahethiopia