Get Mystery Box with random crypto!

#ሊቢያ #ግሪክ እንደ ጣሊያን የባሕር ጠረፍ ጥበቃ መረጃ ፥ ባለፈው ሳምንት የሜዲትሬንያን ባሕርን | TIKVAH-ETHIOPIA

#ሊቢያ #ግሪክ

እንደ ጣሊያን የባሕር ጠረፍ ጥበቃ መረጃ ፥ ባለፈው ሳምንት የሜዲትሬንያን ባሕርን አቋርጠው ወደ #አውሮፓ ለመሻገር በመሞከር ላይ የነበሩ ፍልስተኞች ጀልባቸው ተገልብጦ 1 ህጻንን ጨምሮ 9 ሰዎች ሞተው አስክሬናቸው ተገኝቷል።

15 የሚሆኑ ፍልሰተኞች የደረሱበት አይታወቅም። 22 ሰዎችን ደግሞ መታደግ ተችሏል።

ከላምፔዱሳ ደሴት 50 ኪ.ሜ. ላይ ማዕበል በማየሉ ነው አደጋው የደረሰው። ላምፔዱሳ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ለሚሞክሩ ፍልሰተኞች የመጀመሪያ ማረፊያ ነች፡፡

በሌላ በኩል ፤ ባለፈው ሳምንት ግሪክ የ3 ታዳጊዎችን አስከሬን ስታገኝ ፤ 19 ፍልሰተኞችን ደግሞ ታድጋለች።

ፍልሰተኞቹ ይጓዙበት የነበረው ጀልባ ከቋጥኝ ጋራ በመጋጨቱ አደጋው ሊደርስ የቻለው።

ግሪክ ከአፍሪካ፣ እስያ እና መካከለኛው ምሥራቅ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ለሚሹ ፍልሰተኞች አማራጭ ናት።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia