Get Mystery Box with random crypto!

#ጠብታ_አንቡላንስ በድንገተኛ እንዲሁም መጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዘርፍ የሚታወቀው ጠብታ አንቡላን | TIKVAH-ETHIOPIA

#ጠብታ_አንቡላንስ

በድንገተኛ እንዲሁም መጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዘርፍ የሚታወቀው ጠብታ አንቡላንስ በአዲስ አበባ ለሚገኙ 10 ትምሀርት ቤቶች በዚህ ዓመት የመንገድ ደኅንነት እና የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ሥልጠና እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በሁለት ትምህርት ቤቶች ሥራውን በይፋ የጀመረው ተቋሙ ተማሪዎችን ስለድንገተኛ ህክምና ማስተማር እንዲሁም ሞያዊ ልምድ እና መነቃቃት በመፍጠር ማብቃትን ዓላማው አድርጎ የተቀረጸ ፕሮጀክት መሆኑን የጠብታ አንቡላንስ መስራች አቶ ክብረት አበበ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ያንብቡ : https://t.me/tikvahethmagazine/21985?single

@tikvahethiopia