#ExitExam የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16-27 | TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam
የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16-27/2018 ዓ.ም ይሰጣል።
የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና ከየካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ትናንት ጥር 19/2018 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው መረጃ ገልጿል።
የፈተና መርሐግብሩን ትክክለኛነትና ለዩኒቨርሲቲዎች መድረሱን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።
በመሆኑም የ2018 ዓ.ም ግማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ዕጩ ተፈታኞች የጊዜ ሰሌዳውን አውቃችሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ ተብሏል።
#ExitExam2018 #MoE
Via @tikvahuniversity