Get Mystery Box with random crypto!

Tikvah-University

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvah_university — Tikvah-University T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvah_university — Tikvah-University
የሰርጥ አድራሻ: @tikvah_university
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.60K

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-26 22:29:37
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የተሰጠው ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ ለመሆን እየተጠባበቁ ለሚገኙ ተማሪዎች የጽሁፍ ፈተና እና ቃለመጠይቅ ሊሰጥ ነው።

የጽሁፍ ፈተና እና ቃለመጠይቁ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በመጡ ባለሙያዎች ከግንቦት 24/2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በቡድን 1A and ቡድን 1B የተመደባችሁ ግንቦት 23/2015 ዓ.ም እንዲሁም ቡድን 2A and ቡድን 2B ግንቦት 26/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በምድባቸው መሰረት እንድትገኙ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://moe.gov.et/storage/Books/List%20of%20Applicant%20Students%20For%20UAE%20Scholarship%202023.xlsx

@tikvahuniversity
60 views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 22:29:37
#MoE

በአዲስ አበባ የሚገኙ አምስት ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ነጻ የትምህርት ዕድል ለተማሪዎች ሊሰጡ ነው።

በኢትዮጵያ የሚገኙ አምስት የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች የመክፈል አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ሊያደርጉ ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ከማህበረሰብ ትምህርት ቤቶቹ ኃላፊዎች ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ፤ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶቹ የትምህርት ዕድል ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ለመስጠት የተስማሙት።

ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶቹ የትኞቹ ናቸው?

ሊሴ ገ/ማርያም፣
ጣሊያን ትምህርት ቤት፣
ቤንግሀም አካዳሚ፣
ሳንፎርድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት እና
አሜሪካን ማህበረሰብ ትምህርት ቤት።

@tikvahuniversity
57 views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 22:29:37
ኢትዮ ቴሌኮም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ስማርት የመማሪያ ክፍልን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አስጀምሯል።

ስማርት የመማሪያ ክፍሉ በዩኒቨርሲቲው አራት ኪሎ ካምፓስ መቋቋሙ ተገልጿል።

ስማርት መማሪያ ክፍሉ የዲጂታል የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ተማሪዎች በቨርቹዋል ቴክኖሎጂ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያስችል ነው።

በተጨማሪም መምህራን በቀላሉ ማስተማር እንዲችሉ፣ የንድፈ ሀሳብ ትምህርቶችን በቴክኖሎጂ ቤተ-ሙከራ እንዲደግፉ የሚያስችል ነው ተብሏል።

@tikvahuniversity
51 views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 17:41:10
በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ከ2100 በላይ መምህራን መገደላቸውን የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታውቋል።

ተቋም በትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የተከሰተውን ቀውስ አስመልክቶ ያካሄደውን ቁጥጥርና ግኝቶች ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በጦርነቱ ምክንያት 2146 መምህራን ህይወታቸው ማለፉን በተቋሙ የአስተዳደር በደል መከላከል ዳይሬክተር አዳነ በላይ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ 1700 ተማሪዎች በግጭቱ የተነሳ ህይወታቸዉ ማለፉን ተቋሙ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የሥራ ኃፊዎችና ባለሙያዎች ባገኘው መረጃ ማወቅ እንደቻለ ገልጸዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ በጦርነቱ ወቅት  ከተቀበሩ ፈንጂዎችና ተተኳሸ መሳሪያዎች ባለመፅዳታቸው ቁጥራቸዉ በውል ያልተገለጹ ሰዎች ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውንም አመልክተዋል፡፡ (ብስራት ሬዲዮ)

@tikvahuniversity
159 views14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 12:29:56
#MoE

በ2014 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩና በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማጠናከሪያ ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የሪሚዲያል ፈተና የሚሰጠው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም እንደሆነ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በቀን ግንቦት 15/2015 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰራጨው ደብዳቤ፤ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ፈተናውን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ እንዲሰጡ አሳስቧል።

@tikvahuniversity
313 views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 12:29:56
#AksumUniversity

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለቀድሞ ተማሪዎቹ ኦሪጅናል ዲግሪ መስጠት ጀምሯል።

ኦሪጅናል ዲግሪ ለማግኘት የሚያስፈልጉ፦

የማመልከቻ ደብዳቤ
ከገቢዎች ሚኒስቴር የተሰጠ የወጪ መጋራት የከፈሉበት ማረጋገጫ
የድጋፍ ደብዳቤ (ስፖንሰር ለተደረጉ)

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕትን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለቀድሞ ተማሪዎቹ ከባለፈው ወር ጀምሮ መስጠት መጀመሩ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
207 views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 12:29:56
ዌብሳይት ዴቨሎፐር ለመሆን ዝግጁ ነዎት?

እንግዲያውስ እኛ እርስዎን ለማብቃት ዝግጁ ነን!

በሁለት ወራት ውስጥ ብቻ በዌብሳይት ዴቨሎፕመንት ብቁ ልናደርግዎ ተዘጋጅተናል።

በምዝገባ ላይ እንገኛለን

ለበለጠ መረጃ፦ 0911724462 / 0942049910

አድራሻ፦ ብስራተ ገብርኤል፣ ሽመክት ንግድ ማዕከል ህንጻ 9ኛ ፎቅ ቢ.ቁ. 9/3

ፈጥነው በመመዝገብ ዘመኑ የሚፈልገውን ክህሎት ያዳብሩ።

ኤርሊ ስታርት አይቲ ሶሉሽን

EARLY START IT SOLUTION

Website: www.earlystarttech.com

Telegram: @earlystarttech

TikTok: https://www.tiktok.com/@earlystartitsolution?_t=8caMFQQciE2&_r=1

#onlineclass #technology #webdesign #webdevelopment #earlystart
201 views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 18:53:04
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት አዳዲስ አመራሮች ተሹመውለታል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ብሩክ ከድር (ዶ/ር) የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡

ጸዳለ ተክሉ የኢስቲትዩቱ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም ሀብታሙ ሙሉጌታ (ዶ/ር) የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እንደተሾሙ ከኢንስቲትዩቱ የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ባለፈው ጥቅምት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሳይመደብለት መቆየቱ አይዘነጋም።

@tikvahuniversity
274 views15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 15:15:02
ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ለማቋቋም የሚያስችለው ረቂቅ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍለው መማር የማይችሉ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚያገል ነው የሚል ስጋት በምክር ቤቱ አባላት ተነስቷል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበረሰብ አገልግሎት፣ የፕሬዝዳንቶች ሹመት፣ የኦዲት ስርዓት እና ሌሎች ጉዳዮችን የተመለከቱ ደንብና መመሪያዎች ሊዘጋጁ እንደሚገባ አባላቱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የአዋጁን ፋይዳ ያብራሩት በምክር ቤቱ የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ፤ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ተማሪዎች ጫና እንዳይኖርባቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ በአራት ተቃውሞ እና በ13 ድምጸ ተአቅቦ አዋጅ ቁጥር 1294/2015 ሆኖ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል፡፡

@tikvahuniversity
295 views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 11:05:20
#Update

በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን በተመለከተ መረጃ ያላሟሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲያሟሉ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል።

በስም የተገለጹ 71 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ያልተሟሉ መረጃዎችን በስልክ ቁጥር 0930642235 በተከፈተ የቴሌግራም አድራሻ መላክ እንደሚጠበቅባቸው ባለሥልጣኑ አሳውቋል።

በመሆኑም ተቋማቱ ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከ የመሙያ ፎርም መሠረት እስከ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም የተጓደሉ መረጃዎችን አሟልተው መላክ እንዳለባቸው ገልጿል፡፡

(የተጓደሉ መረጃዎችን መሙያ ፎርም ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
308 views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ